አማርኛ
ለደንበኞቻችን የምናስተላልፈው መልዕክት
ወደ አዲስ አገር መቀየር እንዲሁ ቀላል አይደለም:: ብዙ ሰው እንዲህ ያደርጋል፣ እናም ብዙ ሀገራት
ከሀገራቸው በተሰደዱ ሰዎች ትክሻ የተገነቡ ናቸው፣ ነገር ግን ያ ማለት ሀገር መቀየር በፍጥነት የሚደረግ
እና የሚያስደስት ልምድ አይደለም:: ለመቀየር እና ከአዲስ ሀገር ጋር ለመለማመድ ያለው ውጥረት፣
እንዲሁም ካለፈው ህይወት የምናጣው ብዙ ነገር ወደ ድብርት እና ስጋት ውስጥ ሊከተን ይችላል ይህም
በማንኛውንም የቤተሰብ እና የጥንዶች ህይወት ውስጥ ጭንቀት ያስከትላል::
አብዛኛውን ጊዜ የቋንቋ ችግር ለአዳዲስ ስደተኞች ተግዳሮት ይሆንባቸዋል:: የቋንቋ ችግርም በሚኖራቸው
የማህበራዊ እና የሙያ መስተጋብር ላይ እንቅፋት ከመሆኑም በላይ፣ ተጨማሪ ጭንቀት፣ ለራስ ዝቅ ያለ
ግምት እንዲሁም ከማህበረሰቡ መገለልን ያስከትላል::
ለምሳሌ፤ ልጆች የእኩዮቻቸውን የአኗኗር ዘየ እና ቋንቋን በተሻለ ፍጥነት መላመድ ይችላሉ፣ ነገር ግን
ለእነርሱ ልክ በሁለት የተለያዩ አለማት እንደሚኖሩ አይነት ስሜት ይሰማቸዋል:: የተለያዩ አለማት፡- በቋንቋ፣
በባህል እንዲሁም በእሴት የተለያዩ:: ስደትን አስቸጋሪ ከሚያደርገው አንዱ ገጽታ፣ ስራ መፈለግ ነው:: ይህ
ፈታኝ ሊሆን ይችላል::
EFT እስራኤል ሀገራችን በስደተኞች እንደተገነባች ይገነዘባል፤ እናም የኛ ግብ ጥንዶችን፣ ቤተሰብን እና
ማህበረሰብን በመርዳት የመስተጋብራቸውን ደህንነት በማነቃቃት አማካኝ የስሜት ሁናቴ ላይ እንዲደርሱ
መደገፍ ነው::
-
ስሜትን መሰረት ያደረገ ህክምና ምንድነው?
ስሜትን መሰተት ያደረገ ህክምና ለጥንዶች: የተጀመረው በሱ ጆንሰን Ed.D እና በሌስሊ ግሪንበርግ፣
PhD ከ25 አመት በፊት ነው:: ይህ የአጭር ጊዜ ተሞክሮና የጥንዶች የህክምና ስርዐት በብዛት ምርምር
የተካሄደበት፣ ብዙ ማብራሪያ የተሰጠበት እና በተግባር የተረጋገጠ የጥንዶች ህክምና አቀራረብ ነው::
በክሊኒካዊ ደረጃ ያለው ጉልህ ውጤትም በተለያዩ ማህበረሰቦች ዘንድ ተግባራዊነቱ የተረጋገጠ ነው::
EFT በጎልማሶች የፍቅር ግንኙነት እና አብሮነትን እንዲሁም በፈታኝ ኩነት ውስጥ ያለን ግንኙነት
ስለመጠገንን በተመለከተ በንድፈ ሀሳብ ደረጃ ጠቅለል አድርጎ አቅርቦላችኋል:: የትዳር ትስስር ውጥረት
ውስጥ የሚገባው የአንድ ጎልማሳ መሰረታዊ ፍላጎቶች:- ከአደጋ የራቀ መሆን፣ ደህንነቱ እና ጾታዊ ግንኙነቱ
አደጋ ውስጥ እንደወደቀ በሚሰማው ወቅት እንደሆነ እንገነዘባለን::
ይህ የህክምና ተሞክሮ/ስርዐት ትኩረት የሚያደርገው የእያንዳንዶችን ጥንዶች አጣብቂኝ ውስጥ
የከተታቸውን ዋነኛውን ግትር አሉታዊ መስተጋብር በመንደፍ ስሜታዊ ተሞክሮዎችን እንዲያጤኑት ይረዳል::
ተከታታይነት ባላቸው የማብራሪያ ደረጃዎችም የህክምና ባለሙያው ጥንዶችን ካሉበት የግጭት መረብ
አውጥቶ አዲስ የመስተጋብር ሰንሰለት እንዲፈጥሩ ያደርጋል::
የ EFT ተመራማሪዎች ማሳየት እንደቻሉት፣ በ ጆንሰን 2004 የሴሚናል ጽሁፍ ላይ እንደገለጹት፣
ተያያዥነትን መፍጠር:- ስሜትን ላይ ያተኮረ የጥንዶች የህክምና ተግባር EFT በሚገባ የሚሰራ ሲሆን፣
ዘላቂ ውጤት አለው፣ እንዴት እንደሚሰራ ስለምናውቅ የህክምና ባለሙያዎችን ማሰልጠን እንችላለን
ስለዚህም በብቃት ይከውናሉ እንዲሁም በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እና ችግሮች ዙሪያ መፍትሄነቱ
ይሰራል:: በተጨማሪም ከሌሎች አካላት ጋር ለምሳሌ:- የትስስርን ውጥረት ተፈጥሮ እና የጎልማሶች
የአብሮነትን ሂደት ከሚመርምሩ አካላት ጋር ጎን ለጎን የሚሄድ ነው:: -
የጥንዶች የህክምና ባለሙያ እየፈለጋችሁ ከሆነ
የፍለጋ መስፈርትዎን የሚያሟላ የህክምና ባለሙያ ለማግኘት እባክዎ የ ዳታቤዝ ገጻችንን ይጠቀሙ::
እንዳለመታደል፣ በዚህ ሰዐት በሀገሪቱ የሚገኙት አማርኛ የሚናገሩ EFT የህክምና ባለሙያዎች ውስን
ነው:: ይሁን እንጂ፣ በዝርዝሩ ውስጥ ያሉት ሁሉም የህክምና ባለሙያዎች በጥንዶች ስሜት ላይ ያተኮረ
ህክምና ኤክስተርሺፕ ያጠናቀቁ ናቸው እንዲሁም አብዛኞቹ ተጨማሪ ስልጠና እና በሰርተፊኬት ደረጃ
ስልጠና ያጠናቀቁ ናቸው:: እንዲሁም የ EFT ሱፐርቫይዘሮች ተዘርዝረዋል:: እዚህ የተዘረዘሩት የህክምና
ባለሙያዎች፣ አንዳቸውም የ EFT እስራኤል ቅጥረኛ አይደሉም::eftcisrael@gmail.com
የምትፈልጉትን ነገር ማግኘት ካልቻላችሁ፤ እና ባህልን ግንዛቤ ውስጥ የሚያስገባ የዕብራይስጥ ወይንም
የእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናጋሪ ለማግኘት እርዳታ ከፈለጋችሁ፣ እባካችሁ በዚህ አግኙን : [email]. -
PROFESSIONAL DISCLAIMER: Before you contact any of our member clinicians,
please read this important notice.
ሙያዊ ማሳሰቢያ: የትኛውንም የክሊኒክ ባለሙያ ከማግኘታችሁ በፊት እባክዎ ይህን ጠቃሚ
ማስተዋሻ ያንብቡ::
PROFESSIONAL DISCLAIMER
ሙያዊ ማሳሰቢያ
EFT እስራኤል ስለ ክሊንክ ባለሙያው አባል የግል ልምድ መረጃ ያቀርባል:: EFT እስራኤል እዚህ
በተዘረዘሩት የህክምና ባለሙያዎች ልዩ ክህሎት ወይንም ከተለየ ግለሰብ ወይም ጥንድ ጋር ስላላቸው
የመስራት ችሎታ ላይ አያገባውም:: EFT እስራኤል በማውጫው ላይ ስለተዘረዘሩት የህክምና
ባለሙያዎች ብቁነትን አይመረምርም፣ አይወስንም እንዲሁም አያረጋግጥም:: የዚህ ማውጫ አገልግሎት
በበጎ ፈቃደኝነት የህክምና ባለሙያውን ለመጠቆም ነው እናም EFT እስራኤልን ምንም አይነት ኋላፊነት
አያስከትልበትም::
በምንም አይነት ሁኔታ EFT እስራኤል የዚህ ማውጫ ተጠቃሚ በራሱ ፈቃድ ለሚመርጠው የህክምና
ባለሙያ ለሚደርስበት ጥፋት ተጠያቂ አይሆንም፣ በተዘረዘሩት የህክምና ባለሙያዎች በቀረቡ
አገልግሎቶች ወይም በማንኛውም ሁኔታ በሚደርሱ ጥፋቶች ተጠያቂ አይሆንም:: EFT እስራኤል
በማውጫው ላይ ተዘርዝረው ስለተካተቱት መረጃ ወይም ስለሚከተሉት አገልግሎቶች በተያያዘ ዋስትና
ማቅረብ አይችልምም አያደርግምም::
ሁሉም ከላይ የተካተቱት መረጃዎች በራሱ በህክምና ባለሙያው የሚቀርቡ እና መግለጫው እውነት
እንደሆነ እና ፎርሙ ምንም አይነት ውሸት፣ ማጭበርበር፣ ማታለል ወይም አሳሳች ነገር እንዳልተካተተበት
ራሱ አረጋግጦ የሚልከው ነው:: የህክምና ባለሙያውም ወደ ኢሜይላቸው ወይም ወደ ድረ ገጻቸው
የሚመራ “links” ሊያቀርቡ ይችላሉ:: EFT እስራኤልም ተጠቃሚዎች በቀላሉ ያገኟቸው ዘንድ እነዚህን
“link” የሚያቀርብ ሲሆን ስለ ትክክለኝነታቸው ግን መደገፍ፣ ማጽደቅ፣ መመስከር፣ ማረጋገጫ መስጠትም
ሆነ ወክሎ አይናገርም::
እርስዎ የአዕምሮ ጤና ባለሙያ ሆነው የ EFT ስልጠና ለማግኘት ከፈለጉ:
እዚህ ጋር ስለ ስልጠና አማራጮች የተወሰነ መረጃ አለ:: እንዲሁም ደግሞ የአለም አቀፉን የስሜት ተኮር
ህክምና ማበልጸጊያ ማዕከልን http://www.iceeft.com እንድትጎበኙ እንጋብዛችኋለን::
1. የ EFT መሰረታዊ ኤክስተርሺፕ ላይ መሳተፍ
ስሜት ተኮር የጥንዶች ህክምና የአራት ቀን ኤክስተርንሺፕ በሄርዘሊያ ዘርፈ ብዙ የጥናት ማዕከል
የሚደረግ ሲሆን:: አብዛኛው ትምህርት የሚሰጠው የ ICEEFT ማረጋገጫ ባላቸው አሰልጣኞች ነው::
ይህ ኤክስተርንሺፕ EFT ለመማር እና በ EFT ማረጋገጫ ያለው የህክምና ባለሙያ ለመሆን የመጀመሪያ
ደረጃ ስልጠና ነው:: ትምህርቱም የአዕምሮ ጤና ባለሙያዎችን በ EFT የጥንዶች ህክምና ሙያ ብቃት
ይኖራቸው ዘንድ መሰረታዊ የክሊንካል ክህሎት የሚያስተምር ነው:: በውስጡም ንባቦችን፣ ትምህርቶችን፣
ውይይቶችን፣ የቪዲዮ ምሳሌዎችን እንዲሁም የተሞክሮ ክህሎት ልምዶችን ያካተተ ነው:: -
-
ሁለት የአራት ቀን የዋና ክህሎት ክትትል ላይ መሳተፍ
የ EFT ዋና ክህሎት ስልጠና ክፍለ ጊዜ የ EFT ማረጋገጫ ባላቸው አሰልጣኞች የሚመቻች ነው:: ዋና
ክህሎት የሚያካትተውም ትንሽ ቡድኖችን (ከ 6- 10 ሰዎች) በመሆን ለEFT ትግበራ ጠቃሚ የሆኑ
ክህሎቶችን መማር ነው:: ስልጠናውም በአራት የሳምንት መዝጊያ ጊዜያት የሚሰጥ ይሆናል፣ በየሳምንቱ
ማብቂያ ለ 12 ሰዐታት:: ተሳታፊዎችም የEFT ኤክስተርንሺፕ ማጠናቀቅ የሚገባቸው እና ስራቸውን
በኦዲዮ/ቪዲዮ አቀራረብ ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው::
3. ክሊኒካል ቁጥጥር ማግኘት
በ EFT የግል እና የቡድን ቁጥጥር የ EFT ማረጋገጫ ባላቸው ተቆጣጣሪዎች እና በተመራጭ የቁጥጥር
ድጋፍ ባላቸው የሚሰጥ ነው:: ተቆጣጣሪዎችንም ከዳታቤዝ ድረ ገጻችን መመልከት ትችላላችሁ::
ቴራፒስት የሚፈልጉ ከሆነ ወይም ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በሚከተለው አድራሻ ይፃፉ:eftcisrael@gmail.com
ስለ ስልጠና እድሎች በሚከተለው አድራሻ ይረዱ: ICEEFT.COM
ይህን ድር ጣቢያ መጠቀም በዕብራይስጥ "ውሎቹ እና ሁኔታዎችን" ማንበብን ይጠይቃል.